የኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ብሄረሰብ ማንነት

 
አዉካሺ በዓሽ
የኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ህዝብ ማን ነው? የት ነው የሚገኘው? ታሪኩ፣ ቋንቋው፣ ማንነቱ ምንድን ነው? የሚለውን ከዚህ በታች እንደሚከተለው እዳስሳለሁ። ይህ ህዝብ ከአዲስ አበባ 120 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል። ይህ ህዝብ ከአያቶቻቸው እንደተነገራቸው እንዲሁም የአያቶቻቸው መቃብር እንደሚያመለክተው የተወሰነው ህዝብ የሸርቅ ገደብ ህዝብ ነው። ይህም በአረብኛ ሸርቅ ማለት ምስራቅ ገደብ ማለት በአረብኛ ቁጣ ወይም ቁጠኛ ማለት ነው። የሚያመለክተው ለጦርነት ከተነሳው የምስራቁ ቁርጠኛ ጦር አባል እንደሆነ ነው።
ይህ ህዝብ እ.ኤ.አ ከ 1525- 1560ዎቹ ጊዜ ዉስጥ በመርከብ ከገቡት የጦር አባላት ዉስጥ ነው። ከዚህ ህዝብ ዉስጥ የተወሰነው ብቻ ከመርከብ የገቡ የዘር ግንድ ሲኖራቸው ሌሎች ከአካባቢው ተወላጆች ናቸው። ከዚህ ዉስጥ የኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ወይም ኮኪር ማለት በቱርክ ወይም በአልባኝ አንጀት ማለት ሲሆን፣ የኮኪር ገደባኖ 7 ቤተሰብ ዉስጥ የኡስማን ባሻ ጥላሞ(ቴሌም) ቤተሰብ፣ በጋዞ አነማጅ ከዚብ ቤተሰብ፣ በጋዚ መዘር ቤተሰብ ሌሎችም ማዕረግ የሌላቸው በዚህ በኮኪር ገደባኖ ቤተሰብ ዉስጥ የሚገኙት ማራንኦቶ፣ ደሳ፣ አንቀዲን፣ ዘሬ የቱርክ እና የአልባኝ የዘር ግንድ ያላቸው ናቸው። ሌሎችም የጉታ አዘር ጎሳዎች የቱርክ እና የአልባኝ የዘር ግንድ ያላቸው እንደነ ሰፋቶ፣ ቁርባኖ፣ ደንግዝ እና ሌሎችም በማዕረግ አዛዥነት በኦቶማን ጦር እስልምናን ለማስፋፋት ተሳትፈዋል።
ኦቶማን ከከሰላ ወደብ እስከ ሞምባሳ ወደብ ይቆጣጠር ነበር። የኦቶማን አዛዥ አዝዴ ይመር ባሻ የመንን በአገረ ገዥነት ሲያስተዳድር ቆይቶ እ.ኤ.አ በ1525 ኢትዮጵያ ዉስጥ አቢሲኒያ ባልነበረችበት ወቅት ሃበሻ ተብሎ በሚጠራው ሰሜኑ ክፍል በኦቶማን ንጉስ በሴህ ቃኑኔ ሱለይማን ጃአሞ ትዕዛዝ ከየመን በአርጊጎ በኩል የአሁኑ (ምጽዋ)፣ ቤሉል፣ በርበራ፣ ለየመን ቅርብ የነበሩ ወደቦች ሰሜኑ ክፍል ተቆጣጥሮ ለአመታት አስተዳድሯል። ሰሜን ሃበሻ ሲቆጣጠር የኦቶማን ንጉስ በሴህ ቃኑኒ ሱሌማን በሚያስተዳድርበት እ.ኤ.አ ከ1520- 66 ባለው ጊዜ ዉስጥ ነበር። በኦቶማን የሃበሻ መሬት ተብሎ የሚታወቀው የህዝብ ቁጥሩ በሺህ የሚቆጠረው የሰሜኑ አነስተኛ ክፍል ብቻ ሲሆን፣ ቀሪው የአፍሪካ አካል የህዝብ ቁጥር በሺህ የሚቆጠር በጫካ የተሸፈነ አፍሪካዊያን ጎሳዎች በየቦታው በፒጊሚነት እርሻ እስከታወቀበት ድረስ ኑሯቸዉን በጫካ ዉስጥ ነበር ያደረጉት።
በዚህም በኦቶማን የሚመራው ጦር እንደ ምስራቁ ሽማግሌዎች የዛግዌ ንጉስ የምስራቁን ክፍል ለመዉረር በተከታታይ እያጠቃ እንደመጣ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ እንደ ሃገር ቆማ ያልነበረች ሃገር በዚህም በተለያዩ አነስተኛ ነገዶች እና ንጉሶች ይመራ የነበረ ክፍል በወቅቱ ሃያላን በነበሩ አገራት ፖርቹጋልና ኦቶማን የአለምን የንግድ መስመሮች ለመቆጣጠር በተለይ በባህር ላይ ያነጣጠረ እንዲሁም ሃገራት ለአገሮቻቸው የሚያፈልገዉን ቅመማ ቅመም ንግድ፣ ወርቅ፣ የጦር አባላት ምልመላ፣ ሃይማኖት የማዳረስ፣ ግዛት የማስፋፋት፣ ለቀለብ የሚሆን እህል የሚመረትበትን መርጦ እሱን ማደራጀት ከአላማቸው ዉስጥ እንደነበር ይታወቃል።
በዚህም በባሻ አዝዴ የሚመራው የሰሜን፣ የመካከለኛው፣ የምስራቁን፣ የመዕራቡን ስትራቴጂክ ናቸው ብለው ያሰቡትን ቦታዎች በአብዛኛው ጫካ እና የማንም ያልነበረ መሬት ተቆጣጥረዋል። ሰፊ እና የማይሞከረው የአፍሪካን ጫካ ለመንካት ጊዜው እና የሰው ሃይል አልነበረም። በመረጡት የተወሰኑ ቦታዎች ለዚህም ኮኪር ገደባኖ መሃከለኛ ስትራቴጂክ ቦታ እና ካምፕ ሆኖ ለኦቶማን አገልግሏል።
ይህም ወደ ጎጃም እና ወደ ምስራቅ በርበራ በገደባኞች በርበሬ ማለት የአፍሪካ አፍንጫ ወደብ የሚወስደው መንገድ ላይ ስለሚገኝ እና ቦታው ከደጋ ለመጡት የኦቶማን ወታደሮች ተስማሚ አየርና ከመጡበት የአየር ንብረት ጋር ስለሚመሳሰል ቦታዉን ኡስማን ባሻ በዳኝነት እና በአዛዥነት በኦቶማን ኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር በቆዩበት አመታት ዉስጥ ነበር። በዚህም ከኡስማን በሌሎች የኦቶማን አባላቶች የተወለዱት አሁንም ድረስ ያልተቋረጠ ያልተረሳ የዘር ግንዳቸውን አሞካሽተው ያወሳሉ፣ ለሚቀጥለዉም ትዉልድ ያስተላልፋሉ።
የኮኪር ገደባኖ ሽማግሌዎች ስለታሪኩ ሲናገሩ፣ ከአዉካሽ ኡስማን ባሻ ጥላሞ የሚወለዱ ሃጂ አርጋ በጥላሞ ቤተሰብ ዉስጥ የመጣነው ከቱርክ ነው ሲባል ሰምተናል። ይህ ከገጠር የሚገኘው ህዝብ የእስላም እምነት ተከታይ ነው። የእስልምና ትምህርት የተማረ እና ገበሬ ስለሆነ በቅድሚያ የሚያስበው ለዕለት ኑሮው ስለሆነ የቀድሞ ታሪኩ እና ማንነቱ ለማሳወቅ ጊዜ አልፈቀደለትም ነበር።
ኦቶማን የእስልምና ሃይማኖት ለፈለገ አስልመዋል። ሆኖም ግን በምስራቅ አፍሪካ ካሉት ጋር አለመግባባት እንደነበረ እና እሱም አፋሮች አንዳንዶቹ የኦቶማን ጦር አባላት ክርስቲያን ናቸው በሚል አለመግባባት ነበር። ዛግዌ ወደ ፖርቹጋል መልዕክተኛ ልኮ የጦር እገዛ እስከተደረገለት ድረስ ኦቶማን የሰሜን ክፍል ለ11 አመታት ከተቆጣጠረ በኋላ የፖርቹጋል ጦር አርጊጎ ሲደርስ ከኦቶማን ጦር ጋር ከፍተኛ ዉጊያ አድርገዋል። በመቀጠልም ጦርነቱ በፖርቹጋል መረታት ሲጠናቀቅ ከአባይ በታች ያለው አንዳንድ ቦታዎች በኦቶማን ስር ሆኖ ለብዙ አመታት እንደቀጠለ ስለኦቶማን የተጻፉት መጽሃፎች ይጠቅሳሉ። ለዚህም ፖርቹጋል ሙሉ ለሙሉ አሸንፈዋል ማለት አይቻልም።
በዚህ ሃገር ያለው እስልምና ሃይማኖት በአብዛኛው እዚህ ደረጃ እንዲደርስ የተደረገው በዚሁ በኦቶማን የእስልምና ዘመቻ ነው። በመሆኑም በዚህ እስልምና የማዳረስ ተግባር የተከናወነው ከአዝዴ ጋር ከየመን የመጡ የእስልማና አዋቂዎች አማካኝነት ነው።
በዚህም ዋነኛው የሱፊ እስልምና ተከታይ እና አናጂና መስጊድ መስራች እስልምና እንዲዳረስ ካደረጉት ዉስጥ የነበሩት የኦቶማን ሴህ ሁሴን ሙራድ ናቸው። እሳቸው ከደቡብ ምስራቅ ወደ መካከለኛስ መዕራብ የአሁኗ ኢትዮጵያ ከመፈጠሯ በፊት የእስልምና ሰበካ እንዲዳረስ አድርገዋል።
ከምፅዋ ወደብ ጀምሮ የተቀሰቀሰው የፖርቹጋል እና የኦቶማን ጦርነት አስከፊ ነበር። ጦርነቱ የተካሄደው ኦቶማን ከሚቆጣጠራቸው ወደቦች ተነስቶ እስከ መጨረሻው ኦቶማን ባልተካፈለበት ሽምብራህ ፍሬ እንደ ገደባኖ ሽማግሌዎች የቃላት ትንተና (በገደባኖና ቋንቋ በሃርብ ተሺም) ተብሎ የሚታወቀው ከጦርነቱ ተደበቅ ወይም በሌላ ቃላት ሲብራራ ሺም ማለት በአረብኛ ወይም በገዳባኖኛ ተደበቅ (ብራህ) ብራህ ወይም ሃርብ ማለት ጦር በአረብኛ ሲነበብ እና ሲጠጋጋ እንደሆነ ይጠቅሳሉ።
የምስራቁ አፍሪካዎች ጦሩ በነሱ እንደተካሄደ ሲገልጹ የሽንብራን ፍሬ ጦርነት ብቻ ማለት እንደሆነ ይታወቃል። ሌላው ጦርነት በሁለቱ ሃያላን አገራት በጆርቹጋል እና በኦቶማን ነበር። የኦቶማን ታሪካዊ ጠላት ከነበረው ከፖርቹጋል ጋር በብዙ ጦር ግንባሮች ተፋልመዋል። ከሃበሻው ጦርነት በፊት የኢንዲያን ዉቅያኖስ፣ የቀይ ባህርን የንግድ መስመር ለመቆጣጠር በኢንዶኔዢያዎች በሌሎችም የምስራቁ አካባቢ ግዛትን የማስፋፋት፣ ሃይማኖትን የማስፋፋት፣ ንግድን ለመቆጣጠር በሁለቱ ሃያላን አገራት መካከል ተፋልመዋል።
የምስራቁ ቁጠኛው ጦር መሳሪያ የታጠቀ ከአዉሮፓዊው መሳሪያ የታጠቀ ጋር ነው የተዋጋው። ከቆዳ ቀለሙ ጋር አንድ ከሆነው ከኦቶማን ጋር ነው። ሆኖም ዶ/ አሸም በመጽሃፉ ዉስጥ እንዳሰፈረውበአፋር እና በአፋር ብቻ ፖርቹጋልን እንደገጠመ የገለጸው እዉነታው የራቀ ነው።
የፖርቹጋል ጦር ከ300-400 የሆነው ፖርቹጋላዊያን የያዘ የሰሜን ህዝብ ተዋጊዎች የያዘ ኦቶማን በቁጥር በዉል የማይታወቅ ቁጥር የሃገሪቱን ደቡብ እና ምስራቅ ያካተተ ይዞ በመጀመሪያ ሁለት ጦርነት ዉጊያው ተካሂዷል።
የፖርቹጋሉ ጸሃፊ ምርሴሉ አገሩ ፖርቹጋል ከጦርነት እንደተመለሰ በጻፈው መጽሃፍ ላይ ምላሱ አርጊጎ ወደብ ላይ እንደተቆረጠ የጦርነቱን አስከፊነት ያመለክታል። የኦቶማን ወታደሮች ካምስራቅ ኢሲያ፣ ሙሉ ለሙሉ የአረብ አገራት፣ ደቡብ አውሮፓ፣ የምስራቁ የአፍሪካ ቀንድ ወደቦች እና ቦታዎች ይቆጣጠር ነበር። ኦቶማን ከሚያስተዳድራቸው አገራት ምንም እንኳን እ.ኤ.አ በ1540ዎቹ ሃገራት እንደዛሬ ግልጽ በሆነ ድንበር የተከለለ ባይሆንም በጎሳና፣ በንጉስ ስር ይተዳደር የነበረው አብዛኛው ሃገራት የዛሬው 50 ግዛቶች 1530-1800ዎቹ በኦቶማን ቁጥጥር ስር ነበር።
በዚህም የእስልምና ተከታዮች ቁጥር ዛሬ ላለው 2 ቢሊዮን ህዝብ መሰረትም የጣለው ኦቶማን ነው። ወደዚህ ሃገር የመጡ ወታደሮች በዚሁ ኦቶማን በሚቆጣጠረው ሃገራት የተዉጣጡ ነበር። ከወታደሮቹ ዉስጥ አልባኒያ ጃኒ ስራይ ነበሩ። ለዘብተኛ እስልምና የሚከተሉ አልባኒያን ኦቶማኖች ከአፋር ጋር ከፍተኛ አለመግባባት ነበር። መስማማት ያልቻሉባቸው ምክያቶች በቋንቋ መግባባት አለመቻል፣ የስልጣኔ ክፍተት በአፍሪካዊያኖቹና በሩቅ ምስራቁ ነበር። ከኦቶማን ወታደሮች ዉስጥ በኦቶማን ተቀጥረው ለማገልገል ተፈቅዶላቸው የተቀላቀሉ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ ኦቶማን ወታደሮች ዉስጥ የእስልምና ሱፊ ተከታይ እና ክርስትና እምነት የሚከተሉት ሃይማኖታቸዉን እንደያዙ ለኦቶማን ለማገልገል ፈቃደኞች ነበሩ።
በተጨማሪም የኦቶማን ጦር በአዝዲ የበላይ አዛዥነት ከአፋር ጋር በተፈጠረ መሰረታዊ ልዩነት አፋሮችን በተራ ወታደርነት የያዘ ሆኖም ግን ጦርነቱ በምስራቅ አፍሪካኖችና በኦቶማን ጦር መካከል የነበረ አለመተማመን የጦርነቱን የአንድነት መንፈስ እንዳናጋው እና በመጨረሻም የኦቶማን ወታደሮች ላለመዋጋት እምቢታን እንዳሳዩ እና በጦርነቱም እንዳልተሳተፉ ለሽንፈቱ ዋና መንስኤ እንደነበረ የኦቶማን መጽሃፍ ይጠቅሳል። በተጨማሪም እ.ኤ.አ 1535 የኦቶማን ንጉስ ሱለይማን ጃሞ ሃንጋሪ ዉስጥ ስለሞተ በዚህ ዓመት ኦዘዴ ባሻ ይመር ሃበሻ መሬት ላይ ሞተ። የሁለቱ ቁልፍ ግለሰቦች መሞት ለጦሩ የመዋጋት መንፈሱን እንዳቀዘቀዘው ይነገራል።
በዚሁ ወደ መሃል ሃገር የምስራቁ አፍሪካ ለጤና፣ ለቀለብ፣ ለንጹህ ዉሃ፣ አየሩም ሞቃታማ እና ምቹ ስላልሆነ ጫካ አቋርጠው የዛሬው ኮኪር ገደባኖ የተቆረቆረችው በነዚህ ከአዝዴ ጋር አብሮ ከመጡት በነ ኡስማን ባሻ ነበር። ዶ/ ሃሺም የአልባኒያ ኦቶማን ቴሌም (ጥላሞ) ጋር ቅራኔ እንደነበር ጠቅሷል። የኮኪር ገደናቦ ጥላሞ መሬት ኡስማን ባሻ የመሬቱን ስም በራሱ የመጨረሻ ስም ጥላሞ ብሎ እንደሰየመው በዚህም በኮኪር ገደባኖ በቆየበት አመታት 4 ልጆች እንደወለደ በዚህም ኡስማን ባሻ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም 2 የጦር ማዕረግ ያላቸው ጋዞ ከሲብ እነማጅ እና መዘር ጋዚ ወይም ጋዚ መዘር ሌሎችም ማዕረግ የሌላቸው ወልደዋል። ከቆረቆሩበት እ.ኤ.አ 1555 ጀምሮ ነው ቤተሰብ የመሰረቱት።
የኦቶማን ኮኪር ገደናቦ ጉት አዘር መስራች ኡስማን ባሻ እንደ ሪቻርድ ፓንክረስት ጽሁፍ በድርቅ ወቅት በሰሜኑ ሃበሻ መሬት ከጦርነቱ በኋላ ለንግድ በሚመላለስበት ወቅት ወይም የመጨረሻ የመዉጫ ጉዞ ላይ እንደታየ ዘግቧል። ወደ አፍሪካ ከመጣው በኦዝዴ እና በሌሎች የጦር አዛዦች የተመራው በቆይታው አመታት አገር ለማቅናት፣ ሃይማኖት ለማስተዋወቅ፣ የማንም አገር ባልነበረበት ቦታ ማዕድን በመፈለግ በኩሉ ካፒ፣ ጉሙዝ፣ ሻኪሶ፣ ዲማ አካባቢዎች ተሰማርተው ነበር። በንግድ በመሰማራት፣ በእርሻ ተሰማርቶ ለኦቶማን ጦር ወደ ምስራቁ እህል ይልክ ነበር። እርሻን ያስተዋወቀው ኦቶማን እንደነበረ በተለይ በኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር አካባቢ ይታወቃል።
ሆኖም በጦርነት ለመሳተፋቸው በኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ለወለዳቸው ልጆች የመጣነው (ቱርክቲሊ) ወይም ከቱርክ ነው ሲባል ሰምተናል። የኦቶማን የጦር አባል ከጦርነቱ በኋላ የቀረዉን ወደሃገራቸው ተመልሰዋል። ኦቶማን በመጀመሪያ አለም ጦርነት ከተሸነፈ በኋላ ቱርክ በዴሞክራሲ ስረዓት እየተዳደረች ትገኛለች።
የኦቶማን ጣት አሻራ ይቆጣጠሩ ከነበረው ከሰሜን ክፍል እንዲሁም በኦቶማን በኮኪር ገደባኖ ሰፋ ያለ ነው። የእስልምና መቃብር የሞቱት የተቀበሩት ጢያ ድንጋይ የቀድሞው የኦቶማን ኮኪር ገደባኖ ግዛት የኦቶማን መቃብር ነበር። በመቃብሩ ላይ አላህ የሚል እንደጸጻፈበት እንዲሁም የመርከብ ማሰሪያ ምስል በድንጋዮቹ ላይ ይታያል። በተጨማሪም ርቻርድ ፓንክረስት በመጽሃፉ ኩሉ ቡሊ (ቱሉ ቡሎ) አካባቢ ሁለት የእስላም መቃብር ዋሻ ዉስጥ እንደተገኘ እና የኦቶማን እንደሆነ አንስቷል።
ከኦቶማን አዛዦች፣ ሼሆች፣ ወታደሮች፣ ባለሙያዎች የተወለዱ የራሳቸው የጎሳ መቋሚያ ያላቸው ጋብቻቸው ከአንድ ቤተሰብ ወይም በአንድ ጎሳ ዉስጥ መጋባት ፍጹም የተከለከለ ነበር። በዚህም ከሌላ ጎሳዎች ጋር ተጋብተዋል አሁንም ይህ የጋብቻ ባህል በመተግበር ላይ ነው። የተወለዱት ልጆች ከሌላ ጎሳ ጋር ስለተጋቡ ተክለ ገጽታቸው ከአካባቢው ጋር እንዲቀራረብ አድርጎታል።
ተጨማሪ ማስረጃ ከጢያ መቃብር ድንጋዮች ጎን የኮኪር ገደባኖ፣ ጉት አዘር ቋንቋ የኦቶማን ቋንቋ ነበር ለማለት የሚያስደፍር ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ይህ ቋንቋ Classic ኦቶማን የቀድሞ ቋንቋ በፕሬዘዳንት ከማል በፋረሲ እስከለወጠበት ጊዜ ድረስ የተዉጣጡ የወታደሮች ሃፈራት እና ማንነት የሚያንጸባርቅ ቋንቋ ነው። ይህን ቋንቋ ባጠኑት ሲገለጽ 15-20% ጥንታዊ (Classic) አረብኛ ቃላት እንደያዘ ወይም እንደሚቀራረብ፣ 40% ከተዉጣጡ ወታደሮች ጋር የሚዛመድ ከኩርዲና፣ ከካኔቴ ቱርከኛን ቃላት ጋር ተዛማጅነት አለው። የቋንቋ መዝጊያ (Suffix) አፍሪካ ዉስጥ ከሚገኙ ቋንቋ ጋር የማይገናኝ እንደ ወታደሮች ቋንቋዉም ከባህር ማዶ የመጣ ነው። ከቋንቋ 20,000 ቃላት ዉስጥ 20-30 ቃላት ብቻ ከምስራቅ ቃሉት ህዝቦች ቋንቋዎች ጋር ይመሳሰላል።
ቋንቋው በኮኪር ገደባኖዎች፣ ጉት አዘርኛ፣ በሲዳኦኛ/ ሲያድ ወይም አልሰዳምኛ በአቶማንኛነት፣ በኢስማንኛ ይታወቅ ነበር። አፍሪካዊ የቋንቋ ባለቤት አልነበረዉም። በተጨማሪም ሌላ ያለው ማስረጃ የጎሳ መቋሚያ አስተላለፉና የሃገሩ ሴራ ህግጋቶች ናቸው። ህጎቹ ከሸሪያ ህጎች ጋር የሚቀራረብ በተለይ በጋብቻ ንካ አስተሳሰር፣ በወንጀል ክስ (ኤክ) ላይ የነበረው እና አሁንም ድረስ በስራ ላይ ያለው ባህላዊ ህጎች አንድ ናቸው።
የኦቶማን ኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ማንነት ከሚገኘው ታሪካዊ ቅርፅ በተጨማሪ ማንነቱ ነው። የሰው ጸጉር፣ የቆዳ ቀለም፣ የአፍንጫው ቅጥነት እና ዉፍረት ሳይሆን ማንነት በአብዛኛው ለዚህ ህዝብ በምላሱ ላይ ነው ያለው። ይህ ህዝብ በጉራጌ ዞን ዉስጥ የሚገኘው ህዝቦች ጋር በሰላምና በስምምነት ለአመታት ኖረዋል። ነገር ግን ህዝቦች የተለያዩ ማንነት አላቸው። ሆኖም ማንነታቸው ከሌሎች ጋር ተዳብሎ ይገኛል። በማንነት ጥያቄ ላይ የዚህ ህዝብ አባላቶች ተቃዉሞ ሲያቀርቡ ለአመታት በእስር ቤት ታስረዋል፣ ተገርፈዋል። ሽማግሌዎቹ ለ117 አመታት መታገላቸውን ይገልጻሉ።
የሃገር ሽማግሌዎች በተለይ የኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ሽማግሌዎች ዞኑ ማንነት ዙሪያ በዚህ ህዝብ ሶስት መቋሚያ ካለው ህዝብ አንደኛው የእኛ ያልሆነ በግድ እንድንሸከም የቋንቋው ስምም ሶስት መቋሚያ ሆኖ ሳለ በአንድ መቋሚያ ያለኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ሆኗል። ይህ የተፈጠረው በምስራቅ ከገቡት እና ካልገቡት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ጥናት ሲደረግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በኦቶማን የተሰየመው ኩሉ ቡሊ የሁሉ ቀዳዳ ወይም መሰብሰቢያ በዛሬው ቱሉ ቡሎ ጀምሮ በኦቶማን ከተቆረቆረችው ከተማ (ባል አምበ) በአረብኛ አባ (እምቢተኛ) ሌሎችም በአቅራቢያው የሚገኙ ከተሞች በሙሉ የተሰየሙት በኦቶማን ነው ለዚህም ሃርብ ጩላልቸ) የጦርነቱ ልጆች ከተማ፣ (ጎንግ) የጫካዉን መንገድ ጎ-ኡንገ፤ (ኦማሞ ወንዝ) የመሃመድ ወንዝ ሌሎችም የተራሮች ስም፣ የጎሳ ስም፣ ከኦቶማን በመጀመሪያ የተወለዱት ልጆች ስም፣ የወንዞች ስም፣ የተለያዩ ቦታዎች ስም በሙሉ በኦቶማን የተሰየመ ነው።
እንዲሁም በጉት አዘር 13 ቤተሰቦች/ ጎሳዎች ዉስጥ የሚገኙት ቁርባኖ፣ ኦሌ፣ ሰዳኦ፣ ደንግዝ፣ እሬሾ፣ ቡርቃ፣ ሰፋኦቶ፣ ጎኡምራ፣ ሃደእሮ፣ ኦማኖ፣ ጋርአኖ ናቸው። አንዳንዱ ይህ የኦቶማን ኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ህዝብ ከምስራቅ አፍሪካዎቹ ቢሆን ዘር ተቆጥሮ ይደረስበት ነበር። ነገር ግን አይደለም እንዲሁም አሁን ከሚገኝበት አካባቢዎች ቢሆን ኖሮ ዘር ተቆጥሮ ይደረስበት ነበር። ለዚህም የሚያጠናክረው ከባህር ማዶ በመርከብ እንደሆነና አያቶቻቸዉም ትክክል እንደሆኑ ነው።
ይህ እስልምና ለማድረስና የማንም መሬት ያልነበረዉን ጫካ መንጥረው የመሰረቱት አገር በተለይ ኮኪር ገደባኖና ጉት አዘርን ያቀፈ ነው። የኦቶማን ኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ህዝብ የራሱ በዓላት አለው። በሳምንት ዉስጥ የሚከበሩ በዓላት የሰይድ እና ከድር ቀን፣ ሊቃቅ ቀን፣ ጅላሎ ቀን፣ ኡስማን ቀን ሶስቱ የእስልምና ሃይማኖት በዓላትን ያከብራሉ።
የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን የቀድሞው በአናቶሊ ኦቶማን ወይም ቶሊ ገበያ የኮኪር ገደባኖ ጉት አዘት ህዝቦች የሚገበያዩበት ቦታ እንደ እህል፣ ለቤት አገልጋዮች የስራ እድል የሚሰጥበት፣ ሌሎች የገበያ እቃዎች ከቀድሞ እስከ አሁን ድረስ የመገበያያ ቦታ ነው፤ ሌሎችም የገበያ ቦታዎች አሉ።
ሌላኛው የቀን አቆጣጠር እንደ እስልምና ተከታይ የሂጅራ ካላንደር ነው። ከሁሉም የመጻፍ እና የማንበብ ደረጃ የተደረሰው በዚህ የኦቶማን ኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ቁርአንን (በሎህና በመድ) በጣዉላ እንጨት እና በነገዶች ቀለም መጻፊያ ሲያስተምሩ ነበር። ጠቋሚ ናቸው ተብሎ በወቅቱ ከነበሩት የተጻፉት ታሪክ የተወሰነው በፍየል ቆዳ፣ በሎህ እንደነበር እና በጦርነት ፋታ ሳያገኝ የኖረው ህዝብ ታሪካዊ ቅርፅ እንደጠፋ፣ እንደተሰረቀ፣ ጠቋሚነቱ፣ ባለማወቅ እንደተሸጠ ይነገራል።
ማንነቱን ከሚያንጸባርቁት ዉስጥ የጥያ እና ሌሎችም እንደ ጥያ ትክል በዉስጥ አገር ይገኛል፣ ቋንቋ፣ የጽሁፍ ታሪክ፣ የጎሳው ሴራ፣ የሂጅራ ዘመን አቆጣጠር፣ የጎሳ(መኮዞ) መቋሚያ፣ በተጨማሪም ባህላዊ ሙዚቃዎች ናቸው።
ኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር እ.ኤ.አ ከ 1555 ጀምሮ ጦርነቶች ከጎረቤት ጋር አድርገዋል። ከአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች ጋርም ኮኪር ገደባኖ ከተቆረቆረ በኋላ በድንበር ግጭት፣ በሴት ጠለፋ፣ በንብረት ዝርፊያ ምክንያቶች ጦርነት ተካሂዷል። ከሁሉም ከፍተኛ ዉድቀት በኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ህዝብ ላይ የደረሰው በሚኒሊክ ወረራ ወቅት ነበር።
ህዝቡ በነበረው አነስተኛ የመከላከል አቅም፣ በራሱ ህግ፣ በራሱ የጎሳ አስተዳደሮች፣ ዳኞች ንጉሶች ሲተዳደር በነበረበት ወቅት ነበር። በሚኒሊክ ጦር ሲሸነፍ ቀኝ ገዢው የዚህ ህዝብና መሬት በመቆጣጠር ህዝቡ በራሱ መሬት ጭሰኛ አደረገው። እስከ ኮ/መንግስቱ አስተዳደር ድረስ በሚኒሊክ እና በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ከ10 በላይ በሆኑ ሃገረ ገዥዎች ከፍተኛ በደልና ጭቆና ተካሂዶበት ያረፈውና የተነጠቀው መሬት የተመለሰለት በኮ/ሌ መንግስቱ አስተዳደር ነበር።
በኢማም ኡመር የጥላምው አዉካሽ ኢስማን ቤተሰብ የሚወለዱት ጦር መሪነት ከሚኒሊክ ጋር ለ20 አመታት ቢዋጉም መሳሪያ የታጠቀና በዚህ ህዝብ ዉስጥ የነበሩ ባንዳዎች ከሚኒሊክ ጋር በማበር ኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር ለመጀመሪያ ጊዜ ኡስማን ባሽ ካቋቋሙት ከ1555 ጀምሮ ሃገሩን ሳያስደፍር ይኖር የነበረው በቀኝ ገዢ በሚኒሊክ ስር እንድትወድቅ ተደረገ።
እ.ኤ.አ ከ1809-1965 የነበሩ አገረ ገዢዎች ፊትአዉራሪ ንጋቱ፣ ፊትአዉራሪ ወልዴ፣ ፊትአዉራሪ ረዲ፣ ደጃዝማች ብሩ፣ በደጃዝማች አበራ ብሩ፣ በፊትአዉራሪ ሳህለ ጊዮርጊስ፣ በፊትአዉራሪ ወልዴ፣ በፊትአዉራሪ በየነ፣ በፊትአዉራሪ ባልቻ ሳፎ፣ በቀኝአዝማች አመልጋ፣ በቀኝ አዝማች ወልደሄር፣ በቀኝ አዝማች አምባየ ቤኛ፣ አርዕስት የሌላት ጊፍቲና አየለች በከፍተኛ በደል ማንነቱን፣ ታሪኩን፣ ባህሉን እና ቋንቋዉን እንዲያጣ የተደረገበት በ74 ዓመታት ዘመን ነበር።
ይህ ህዝብ በኮ/ሌ መንግስቱ አስተዳደር ያለህዝቡ ፍላጎት እና ጥያቄ በጨቦ እንዲካተት ተደረገ፤ በመቀጠልም በወያኔ/ኢህአዴግ አስተዳደር በጉራጌ ዞን እንዲካተት ተደረገ፤ በዚህ በቋንቋ፣ በታሪክ፣ በባህል ከሚገናኘው በዞኑ ዉስጥ ከሚገኘው 6 ብሄረሰቦች ጋር በዚህ ዞን እንዲቀላቀል ሲደረግ ለዚህም የሰሜቲክ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆኑት የዞኑ ብሄረሰቦች ዉስጥ ከሶዶ ጉራጌ፣ መስቃን ጉራጌ፣ ሰባት ቤት ጉራጌ፣ ስልጤ ጉራጌ የዛሬው ገደባኖ ጉት አዘር ጉራጌ ጋር በባህል፣ በአመጋገብ በተወሰነ ደረጃ በቋንቋ ይቀራረባል። በኑሮውን ላይ በኮኪር ገደባኖ ጉት አዘር መሬት ላይ እምብዛም አይን ዉስጥ የሚገባ እድገት የለም። የህዝቡ ቁጥር በወረዳው ውስጥ የሚኖረዉን፣ በጎረቤት ዞኖችና በጎረቤት ክልሎች፣በአዲስ አበባ፣ በተለያየ የአገሪቱ ምስራቅና ደቡብ ክልል ዉስጥ እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው በአረብ ጋር የሚኖረው ጨምሮ የህዝቡ ቁጥር በግምት አምስት መቶ ሺህ እንደሚደርስ ይታወቃል። ከተለያዩ ብሄረሰቦች ጋር የተጋባው ይህ ህዝብ በተለያየ ወቅት በነበረ ጦርነት በስደት ቦታዉን ትቶ እንዲሸሽ ተደርጓል።
የግል እና የጋራ ማንነት ያለው ይህ ህዝብ በመጀመሪያ የግል ማንነቱን የሚገልጸው ለጎሳው በሁለተኛ ደረጃ የጋራ ማንነቱ የሚገልጸው ኦቶማን ባዋቀረው በ7 ጎሳ፣ ይህም በኮኪር ገደባኖነት፣ በ13 ጎሳ በጉት አዘርነት። ከዚህ ዉጭ ከግሉና ከጋራ ማንነቱ ዉጭ ሶስተኛ እና አራተኛ ማንነት ስም አልነበረዉም ሊኖረዉም አይችልም። የማንነቱ ጥያቄ ሲነሳ በሶስቱ የኮኪር ገደባኖ፣ ጉት አዘር ህዝብ መካከል አለመግባባት ስለተፈጠረ በተለይ ሁለተኛው ማንነት ላይ አወዛጋቢና ምርጫ በአንዱ የተጫነበት ማንነት ስለመጣበት ሶስተኛ ማንነት እንዲይዝ የተገደደበት ጊዜ ነበር።
በአራተኛው ማንነት እሱም በመጀመሪያ በጎሳው፣ በሁለተኛ ደረጃ የጋራ መቋሚያ ማንነት፣ በሶስተኛ የእሱ ማንነት በሆነው የጉራጌ ዞን ማንነት በዞኑ ማንነት፣ በአራተኛ ደረጃ እሱ ባልመረጠው በክልሉ ማንነት እንዲጠራ ተደርጓል። በኦቶማን ሲቋቋም ባዶ መሬት እና ባለቤት ያልነበረው ጫካ (በገንዥሞ) መጥረቢያ መንጥሮ ያቋቋመው ግዛት ሰፊ እንደነበር በአገር ሽማግሌዎች ይነገራል። አብዛኛው ግዛቶቹን ያጣው በቦረና ጦርነት ጊዜ እንደነበር ታሪክ ያትታል።
ቅዳሜ ሃምሌ 4 ቀን 2012 ዓ.ም